Home / ARTICLES / ሰሚ አልባ ተሃዝቦት

ሰሚ አልባ ተሃዝቦት

1.ቅጣቱን በመተው ገልጦት ይሆን?

ቤተክርስቲያንን አንስቶ የሚወያይ አሊያም የሚያስብብ ሰው ስለተሰገሰጉት ‘በሽታዎች’ የማያነሳ ከሆነ ከእውነት ስልታዊ ማፈግፈግ ላይ መሆን አለበት። ዘመኔን አይቼ እንዲህ የማስብበት ጊዜ ላይ ደርሻለሁ።ምናልባት ያለንበት ሁኔታ እግዚያብ ሔር ቤተክርስቲያንን እየቀጣ ይሆን? አላውቅም። እግዚያብሔር ከቀናው ጋር ቀና ከጠማማው ጋር ደግሞ እንዲያው ነኝ ያለ፣ ስንጣመምበትና ከፍቃዱ ለመራቅ በመፈለጋችንፍላጎቶቻችንን የሚነግሩንን ሰዎች እየሰጠ ራሱ ከራሱና ከፈቃዱ አ ውጥቶን ይሆን እላለሁ። ስለስሜታችን ብቻ የሚጨነቁትንስ እንደማህበር ‘መንፈሳዊ እብደት’ ላይ ስላለን፣ ጆሮዎቻችንም ያለ’ነሱ መስማትስለማይፈልጉ በላያችን ላይ ‘ጌታና ነቢያት’ ፓስተርና ሐዋሪያት’ አድርገን ሾመናቸው መሆኑን ማመኑ አይከፋም። ከዚህ በላይ ምን ቅጣት አለ? የሚፈልጉትን ከማድረግ በላይ፣ የሚወዱትንስ ከመስማት ሌላ ምንፍርጃ አለ ጃል ?!

ብዙ ጊዜ ስሰማው ማስተወሉን ከማከብርለት ሰው ጋር እንደአሸን ሰለፈሉት ‘ነቢያቶችና ተአምራታዊያን’ አንስተን ስናወ ጋ የላኝን አልዘነጋውም። ”ቤተክርስቲያን ሄጄ እግዚያብሔር ባለሁለት ፎቅ ቤት ባለቤትእንደሚያደርገኝ፣ መኪና በመኪና ላይ እንደሚሸልመኝ ነግሮኝ፣ ስልክ ቁጥሬን አንብቦልኝ ከሄደ ስቅስቅ ብዬ አለቅሳለሁ ምክንያቱም እግዚያብሔር ስለነፍሴ ግድ ባይለው ነውና” እለኝ።

ለኔ ትልቁ ቅጣት እግዚያብሔር ከሃጢያተኛ ማህበር ጋር ተስማምቶ መንጋው እንደልቡ እንዲሆን ሲፈቅድ ማለት ነው። ስ ለዚህም እነዚህን ‘ለመንጋው የማይራሩ አውሬዎች’ የሰጠን እሱ ቢሆንስ? ሊቀጣን! ከቀናው ጋርቀና ከጠማማው ጋር ደሞ እንደዚያው ነኝ ብሎ የለ? ተጣመን ፊቱን አዙሮብን የራሳችንን ጌቶች ሰቶናል ባይ ነኝ። ‘አለ’ ከሚሉ ዝማሬዎች ውጪ ስለምን የመኖሩን (በመሃከላችን) ዱካ ጠፋ? መቼም ከበዛ ጉድፋችን ጋር አብሮ አለ ማለት ድፍረት አይሆንም? የዮሐንስ ራዕይ ላይ በአስተምህሮና በስነምግባር ምክንያትካልተስተካከላችሁ ‘እተፋችሃለሁና እተዋች ሃለሁ’ ተብለው የለም እንዴ? አሁንስ ትቷቸው በትዝታ ቅኝት ለቱሪዝም ግልጋሎት እየዋሉ አይደሉምን?

I think God is not deceived by the contemporary Christian culture!

ከቱሩፋኑ ጋር የሚያገናኘውን ድልድይ እንዲያይ እይናችንን አብራ፣ አጥራ!

2. መዝናኛ ማዕከላት

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው የክርስትና አይነት የግለሰቡን ሰነልቦና በመገንባትና በተለያዩ መንገዶች ምዕመና ኑን ከማዝናናት አያልፍም። ገሚሱ በመዝሙር ያሻው ደግሞ በትንቢትና በጠማማ ትምህርትየሰውን ስሜት ለማነቃቃት ይ ሞክራሉ። ይህንን ማነቃቃት መንፈሳዊ ቅብ ሊቀቡትም ይጥራሉ፤ መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ እንደሚባለው ማለት ነው።

3. መንጋ ወዲህ እውነት ወዲያ

ክርስትናችን በተነሳ ቁጥር በጣም በርከት ያሉ አሳሳቢ ነገሮች አብረውት ይነሳሉ። ከስህተት ትምርት እስከ ስህተት ልምም ድ፣ ከአፍቅሮተ ነዋይ እስክ ፍትህ ጠልነት፣ ከግዴለሽነት እስክ ባለንጀራን አለመውደድ። ከ-እስከ እየተባለ ብዙ ነገሮችን እይነቀሱ ማውጣት አሰላሳይነት የማይጠይቅብት ዘመን ላይ ደርሰናል። ብዙዎቹ ትኩረት አግ ኝተው በአግባቡ እየተመለሱ ነው ለማለት ቢያስቸግርም ሌላ የጠመመውን ለማቅናትእንቅፋት የሆነ ነገር እንዳለ ግን ተዘን ግቷል፣ መንጋው። መደዴው መንጋ!

ብዙ ሰው የስህተት መምህራኑና ኢሞራል የሆኑት ላይ ብቻ ትኩረቱን አድርጎ የመንጋውን እውነት ጠልነት ረስቶታል። መንጋው እውነትን ምን ያህል እንደሚጠላ ማወቅ የሚፈልግ ምዕመናኑ መሪዎቻቸው ስህተታቸውሲጋለጥ እንዴት ሊሸፍ ኑላቸው እንደሚጥሩ ማየት በቂ ነው የሚከተሏቸው ሰዎች በክርስቲያናዊ እውቀት ተሞግተው የሚያራምዱት ልምምድና ትምህርት ፉርሽ መሆኑን እንኳ ቢያውቅ መንጋ መንጋ ነውና ከተሳሰቱትጎን መሰለፍን ይመርጣል። ስለዚህ ስህተተኞቹ ሲወቀሱ አብሮ መወቀስ ያለበት አውቆ ለመታለል በተጠንቀቅ የቆመው ህዝብም ነው(ህዝብ ልክ ነው የሚባለው ፖለቲካ ላ ይ ብቻ ይመስለኛል)። መምህራኑንና የመድረክተወናዮቹን በላዩ ላይ የሾማቸው ህዝቡ ነውና አብሮ መወቀስ አለበት። ወቀሳ ለአሳሳቾቹ ብቻ ሳይሆን የመሪዎቻቸውን ስህተት ለመደገፍ ቃል ገብቶ ላነገሳቸው መንጋም ይመስለኛል።

በነገራችን ላይ መንጋውና መሪው ተመጋጋቢ አይነት ሚና አላቸው። መንጋው የሚፈልገውን የስነልቦና ግንባታ ሲያገኝ መሪዎቻቸው የሃብትና የዝናን ግንባታ ያገኛሉ። መደጋገፍ ይሉሃል እንዲህ ነው! በጣምየሚገርመኝ ግን የዚህን መንጋ በአ ግባቡ የተረዳ ሁሉ መንጋውን ሲያይ እንደፓቭሎቭ ውሻ ለሃጩን እያዝረከረከ ለፈለጣ ሲያመቻቸው ሳይ ነው።

ለምን መንጋውን መናገር ፈለኩ? ምክንያቶቼ እነዚህ ናቸው፤

1 የስህተተኝነት ጅራፍ የሚገባው ለመሪዎቻቸውና ዘማሪዎቻቸው(አስጨፋሪዎቻቸው) ብቻ ሳይሆን መንጋውም ላቅ ያለ ድርሻ አለውና ትችቱን እንዲቀበል ነው።

2 እንደዚህ አይነት መንጋ ውስጥ ተሃድሶ አይታሰቤ መሆኑን ለማስታወስ ያህል ነው። ብዙ ጤናሞች ‘ጤናማ’ ተሃድሶን በ ቤተክርስቲያን የሚሻበት ዘመን ላይ እንዳለ አውቃለሁ። የሃገሬ መንጋ ግን ለተሃድሶ የሚሆንአይመስለኝም።

ምክንያት አንድ፤ እውነትን አይፈልጋትም። ‘ካሪዝማቲካዊነት’ ገዝግዞ ጥሎታል። ‘የካሪዝማቲማቲካዊነት’ ባህሪ ምዕመናን ከቃሉ እውነትና ከመሰረታዊ አስተምህሮ አፋቶ በመሰለኝና ተሰማኝ ላይ ማደላደል ነው። ስለዚህመሰለኝ፣ ታየኝና ተሰማኝ ላይ የቆመ መንጋ አይታደስም፤ ይመስለኛል።

ምክንያት ሁለት፤ ቀለም አልባ መንጋ ነው። የትኛው መሰረት ላይ እንደተመሰረተ በውል ስለማይታወቅ ለተሃድሶ ዘመን ሩ ቅ ይሆናል። መንጋው የጭቃም፣ የአለትም አሊያም የሲሚንቶ ላይ መሆኑ ከመጀመሪያውኑአያስታውቅም(የመጀመሪያዎ ቹ ያበላሹት ከሌለ፣ የኔ ትውልድ ብቻውን የወቀሳ ናዳ ስልምን ይሸከማል?)። ቀለምና መሰረት አልባነቱ የተሃድሶ ተስፍን አርቆ ለመስቀል ሌላ አማራጭ ይሆነናል።

ምክንያት ሦስት፤ መንጋውን በቅጡ ለተረዳው በአንድ እውነት ሳይሆን በርከት ባሉ እውነቶች ላይ እምነት እነዳለው ይገነ ዘባል። ጤናማውንና ጠማማውን ትምህርት እኩል ያስኬዳቸዋል። ልዩነታቸው ብዙምአይታየውም። ሁሉም የእግዚያብሔ ር ስም እስካላቸው ድረስ ልክ ናቸው ብሎ ያስባል። በቤተክርስቲያንም ደረጃም ቢሆን በድሮዎቹና በአዲሶቹ መሃል የጎላ ልዮነት አለመኖሩ ሁሉንም ለመቀበል ባይገደድ ነበርየሚያስገርመው (በቅንፍ ሌላ ሃሳብ፤ አዳዲሶቹን ብቻ ከመውቀስ ባሻገ ር የቀድሞዎቹ በአግባቡ ተመርምረው ያውቁ ይሆን? ከአዳዲሶቹስ ‘በሽማግሌ’ ከመመራት በምን ይለያሉ?)።

ምክንያት አራት፤ ባለፉት አስር አመታት የተቀላቀለውን መንጋ ልብ ላለ ደንገጥ ማለቱ አይቀርም። የትኛው ወንጌል ተሰብኮ እንደመጣ ስለማይታወቅ (‘ሃብታም የሚያደርግና ከሆስፒታል የሚያስቀር ጌታ ከሆነማእንዴት ጌታን አልቀበልም’ ብ ሎ የሽሙጥ የተናገረኝን ወዳጄን አልረሳውም፣ ሲያቀብጠኝ አጉል ቸርች ወስጄው ሂሴን ውጬ ተመልሻለሁ) ሌላ የተሃድ ሶ ደንቃራ የማይሆንበት ምክንያት አይታየኝም።

ለማንኛውም ግን ደረጄ ከበደ (ዶ/ር) የዘመረውን መድገሙ አይከፋም፤ ለኛስ ከሌላ ስፈራ መዳን/ ይሆንልናል።

4. የክርስትና ዋና ጠላት

ክርስትና ከተቋማዊቷ ቤተክርስቲያን በላይ የሚያቆሽሸው እንደሌለ የቤተክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል። ከስህተት ትምህርት በላይ፣ ከኢአማኒያን ትችት በላይ፣ ከሌላ ሃይማኖቶች ሙግት በላይ ክርስተና የተቋማዊቷንቤተክርስቲያንን ጥቃት መከላከ ል እይችልም። ቤተክርስቲያን ‘ተቋማዊ’ በሆነች ጊዜ ክርስትና ላይ ትከፋለች፣ የክርስትናን መሰረታዊ እምነትንም ትንዳለ ች። ክእውነተኛው ወንጌልም ታፈነግጣለች፤ ጥቅሟንእውነተኛው ወንጌል አያስጠብቅምና። ያፈነገጠውን ግን ይመስጣታ ል። ተቋማዊቷ ቤተክርስቲያን ደረጄ እንደታዘበው ‘በበጎቹ መግቢያ የገቡ ተኩሎች’ ስብስብ ናት።

Check Also

ሲደክም ከዋለ መብሉ የታለ?

መሪ ጥቅስ፡ – ” የሚደክመው ገበሬ ፍሬውን ከሚበሉት መጀመሪያ እንዲሆን ይገባዋል።” (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:6) …

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *