Home / ARTICLES / ከእውነት ርቀህ እየሄድክ ነው?

ከእውነት ርቀህ እየሄድክ ነው?

በአሉላ ጌታሁን

Some have wandered away… (1 Timothy 1:6)

ከእነዚህም አንዳንዶች ስተው፥ … ወደ ከንቱ ንግግር ፈቀቅ ብለዋል። (1 ጢሞቴዎስ ፩:፮)

ማንም ሰው እውነትን በአንድ ጊዜ ለመተው አይወስንም። ብዙውን ጊዜ የሚሆነው፤ ሰዎች ካላቸው እምነት እና እውነት ፈቀቅ ነው የሚሉት፤ ይህም ደግሞ የሚሆነው፣ ቀስ በቀስ፤ በሂደት ነው።

ታዲያ ለማፈግፈግ ተጋላጭ እንዳንሆን፤ ለዚህ አደጋ ንቁ መሆን አለብን። ምናልባትም ከእውነት ፈቀቅ እያለ ያለ ሰው እናውቅ ይሆናል እናም እግዚአብሔር ይህን ሰው ለመመለስ እና በእውነት ውስጥ እንዲተከል ለማገዝ ሊጠቀምብን ይችላል።

* የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን እንመልከት! *

አንድ ሰው ከእውነት ወጥቶ የመጓዝ አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሆነ የሚያሳዩ አንዳንድ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች አሉ። እነዚህ አሁን የማነሳቸው ጥያቄዎች፤ ምልክቶችን እንድናይ ይረዱናል።

  • ሁልጊዜ አዲስ ነገርን ነው የምንፈልገው?
[They] devote themselves to myths and endless genealogies. (1 Timothy 1:4) (1 ጢሞቴዎስ ፩:፬)

ይህ እውነት ከሆነ፤ አደጋ ውስጥ እንደሆንን ማሳያ ነው። ጳውሎስ “አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ” እያለ የሚናገረው ይህንኑ ነው! ሁልጊዜ አዲስ ነገርን መፈለግ! በክርስቶስ ላይ ጥልቅ የሆነ መሰረት ያላቸው ሰዎች ሁልጊዜ በእርሱ ይደሰታሉ፤ ይረኩማል። ለእነዚህ ሰዎች እርካታ፤ ከተልያዩ አዳዲስ ነገሮች አይደለም የሚመጣው፤ ከራሱ ከክርስቶስ እንጂ!

  • እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ማውራት ብቻ እንፈልጋለን?

They have turned to meaningless talk. (1 Timothy 1:6) (1 ጢሞቴዎስ ፩:፮)

እንደዚህ አይነት ሰዎች፤ ነገሮችን እንዴት ማድረግ እንዳለብን እና እንዴት ማድረግ እንደሚገባን በሚገባ ይነግሩናል፤ ነገር ግን የሃይማኖት እና የእምነት ምሰሶቻቸው ያልተቀደሰ ሕይወትን የተሸከመ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን፤ መታዘዝ የሚገባን ባለስልጣን ቃል ሳይሆን፤ ለመወያየት እንደቀረቡ ሃሳቦች ስብስብ የምመለከት ከሆን፤ ከእውነቱ የሚሸሽ አይነት ሰው ምልክት እያሳየን ነው።

  • መማር ከፈለግ በላይ ማስተማርን እንፈልጋለን?

They want to be teachers. (1 Timothy 1:7) (1 ጢሞቴዎስ ፩:፯)

እነዚህ ሰዎች ደግሞ በቤተክርስቲያን ውስጥ “ሥልጣን” ያላቸው ሰዎች ናቸው። ለመማር ከመፈለግ የበለጠ መምህራን መሆንን ይፈልጋሉ። ማስተማርን የምንወድ፤ ነገር ግን ለመማር ፈፅሞ ፈቃደኛ ካልሆንን፤ አሁንም ከእውነት የመራቅ አደጋ ውስጥ ነን።

  • የራስ-መተማመናችን ከምናውቀ እውቀት በላይ የበለጠ ነው?

They want to be teachers of the law but they do not know what they are talking about. (1 Timothy 1:7) (1 ጢሞቴዎስ ፩:፯)

እነዚህ ሰዎች ከፍተኛ ክብደት ያለው ትልልቅ ድምፅ ያሏቸው ቢሆኑም ጳውሎስ ግን እነዚህ ሰዎች ስለ ምን እየተናገሩ እንደሆነ እንኳን እንደማያቁ ነው የሚናገረው! ይህ እውነት ብዙዎቻችን የገጠመን ይመስለኛል።

በእውነት ውስጥ ያልጠበቀ ስር-መሰረት ያለው ሰው፤ የሆነ መጽሐፍ ሲያነብ ወይም የሆነ ንግግርን ሲያደምጥ በጣም ይደሰታል። በድንገትም በዚች ባገኛት ጥቂት እውቀት፤ ከመምህሩ የበለጠ እንደሚያውቅ ይሰማዋል። እሱም ቤተክርስቲያን ምን እንደሚያስፈልጋት እና ምን ማድረግ እንዳለበት እሱ ብቻ በሙላት የሚያውቅ ይመስለዋል።

ያገኘውንም “እውቀት” ለማስተማር እና ለመናገር መድረክ ሊሰጠው እንደሚገባ ያስባል። ነገር ግን ሰዎች “ግኝቱን” ሳይቀበሉት ሲቀር፤ ግትር፣ ቁጠኛና ጠበኛ ይሆናል። ” እውነትንም” በትክክል የሚያየው እርሱ ብቻ እንደሆነም ይሰማዋል። እሱ ያላየው አንድ ነገር ግን እርሱ ራሱ ከእውነት እየራቀ መሆኑን ነው።

* ታዲያ እንዚህ ምልክቶችን ካገኘን እንዴት መመለስ እንችላለን? *

The goal of this command is love, which comes from a pure heart and a good conscience and a sincere faith, some have wandered away from these… (1 Timothy 1:5-6) (1 ጢሞቴዎስ ፩:፮)

የዚህም ትዕዛዝ ዋና ግብ እና ፍፃሜ፤ ንፁህ ፍቅር ነው። ይኸውም ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና፣ ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው።

ታዲያ እንዴት ነው በእውነት ተተክለን በመቆየት፤ በፍቅር እያደግን መሄድ የምንችለው? ይሄስ ፍቅር ከየት ነው የሚመጣው? ፍቅር እየሰፋ የሚሄደውስ እንዴት ነው? እንዴትስ ነው በቤታችን፣ በስራ ቦታችን፣ በትምህርት ቤታችን እና በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እውነተኛ አፍቃሪ ሰው መሆን የምንችለው?

  • መጀመሪያ፤ ፍቅር ከንጹህ ልብ ነው የሚመጣው!

“ንጹህ” የሚለው ያልተከፋፈለ/ያልተለያየ ለማለት ነው። ያዕቆብ “ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል…” ይላል በ(ያዕቆብ 1፥8)። ንጹሕ ልብ እንዲሰጠን እግዚአብሔርን እንጠይቅ። “…ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ።” (ቆላስይስ 3፥1)። በክርስቶስ ላይ ጠንካራ እምነት እና ተስፋ ብሎም በክርስቶስ ላይ ጥልቅ ፍቅር እምዲኖረን እግዚአብሔርን እንጠይቅ። ከዚያ በንፁህ ፍቅር መውደድ እንችላለን። እውነተኛ ፍቅር ከንጹህ ልብ ይመጣልና!

  • ፍቅር ከመልካም ሕሊና ይመጣል!

መልካም ሕሊና፤ ከእግዚአብሔር ጋር ያረፈ ህሊና ነው። በህይወታችን እንዲቆይ የፈቀድንለት ኃጢአት አለ? ካለ፤ ሕሊናችን እረፍት አይኖረውም። ያላረፈ ሕሊና፤ የተበሳጨ፣ ተናዳጅ እና መከፋፈል ያለበት ሰው ያደርገናል። ስለዚህ ከክርስቶስ ከራሱ በሚሆን መታጠብ፤ ንጹሕ ሕሊና ማግኘት ይገባናል። ከዚያ መውደድ እንችላለን! ፍቅር የሚመጣው ከመልካም ሕሊና ነውና!

  • ፍቅር ከእውነተኛ እና መልካም እምነት ይመጣል!

እውነተኛ እምነት ማለት፤ በእውነት ክርስቶስን የሚታመን እምነት ማለት ነው። መታመን ብቻም አይደለም። እምነቱም በስራ ይገለጣል! በህይወታችን ማንኛውንም አይነት ነገር ቢደርስም እናምነዋለን። በሠርግ ቀን እናምነዋለን፤  በቀብር ሥነ ሥርዓትም እንታመነዋለን። በሁሉም ነገር በክርስቶስ ልናምን ይገባናልና!

“…ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።” (1ኛ ጴጥሮስ 1፥7)። ጴጥሮስ ቀጥሎ የሚናገረውን ታስታውሳላቹ? “እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ…” ፍቅር ከእውነተኛ እምነት ይመነጫል።

* እነዚህ ሁሉ ከክርስቶስ [ብቻ] የሚመጡ ነገሮች ናቸው! *

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ንጹህ ልብ፣ ንጹሕ ሕሊና እና ቅን እምነት ሊሰጠን ይችላል። ለዚህ ነው የሞተውም!

ተፀፅተን ንስሃ ከገባን እና እውነተኛ እምነት ካለን፤ ወደ እውነት መመለስ እንችላለን!

  • ይህ ነው የወንጌል የመለወጥ ኃይል! • [ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ ዳግመኛ እስክትመጣ ድረስ ቤተክርስቲያንህ በእውነት ላይ ተተክላ አንተን እየመሰለችን የምታድግ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ውዳሴና ክብርን ሁልጊዜ ላንተ የምታቀርብ ቤተክርስቲያን ታደርገን ዘንድ እንለምንሀለን። አሜን! ]

Check Also

ሲደክም ከዋለ መብሉ የታለ?

መሪ ጥቅስ፡ – ” የሚደክመው ገበሬ ፍሬውን ከሚበሉት መጀመሪያ እንዲሆን ይገባዋል።” (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:6) …

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *