Home / ARTICLES

ARTICLES

ተቀብቼአለሁ!

በአሳየኸኝ ለገሰ በእድሜዬም ሆነ በመንፈሳዊ ሕይወቴ ‹‹ልጅ›› በነበርኩበት ወቅት፤ አንዳንድ ሚስጥር የሚገለጥላቸው (መገለጥ ያላቸው) አገልጋዮች ይህን ሲሉ ከምንም ነገር በላይ እደሰት ነበር፤– “ዛሬ በዚህ ጉባኤ መካከል በልዩ ቅባት የምትቀቡ ሰዎች አላችሁ!!” –ሲሉ— አቤት! ‹ያ ሠው እኔ እሆን ይሆን!?› እላለሁ፡፡ በልዩ ቅባት መቀባት ማለት እንደነርሱ ምስባኩን ተቆጣጥሮ መድመቅ እንደሆነ አስብናም፤ ቀን …

Read More »

አማራጭ ድልድዮች!

አማራጭ ድልድዮች! በአሳየኸኝ ለገሰ ሪቻርድ ፎስተር “the religion of the mediator” ሲል ይጠራዋል፤ አንዳንድ “አገልጋዮች” በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ልዩ “የስልጣን እርከን” እንደተሰጣቸው የሚታሰብበትን ስርአት፡፡ እነዚህ ሰዎች ልዩ ልዩ መገለጫዎች አሏቸው፡፡ ሲጀምሩ፣ እግዚአብሔር በተለየ መንገድ ራሱንና ቃሉን እንደገለጠላቸው አድርገው ራሳቸውን በማቅረብ ይጀምራሉ፡፡ ቃሉን ከነአካቴው ዘግተው በግላቸው “መንፈስ ቅዱስ ገለጠልን” ያሉትን ትኩስ …

Read More »

በቤተክርስቲያን ውስጥ ችላ እየተባሉ የመጡ የጋራ ኃጢአቶች!

በቤተክርስቲያን ውስጥ ችላ እየተባሉ የመጡ የጋራ ኃጢአቶች! ፩ – የሀሰት ምሥክርነት ሁላችንም “ኃጢአተኞችነን ነን”፤ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በዚህ ጉዳይ በጣም ግልጽ ነው (1ኛ ዮሐንስ 1፥8-10)። ይህ ማለት ግን፤ ኃጢአተኞች ሆነን የመቀጠልን ነፃነት አለን ማለት አይደለም! ነገር ቀላል አርገን የምናያቸው ኃጢአቶች እንዳሉ ግልፅ ነው። ከነዚህም ውስጥ አንዱ የሀሰት ምሥክርነት ነው። በምንም …

Read More »

ሲደክም ከዋለ መብሉ የታለ?

መሪ ጥቅስ፡ – ” የሚደክመው ገበሬ ፍሬውን ከሚበሉት መጀመሪያ እንዲሆን ይገባዋል።” (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:6) የመልእክ ዋና ሐሳብ ፦ “የግብርናውን ወቅት ለይቶ በማወቅ፣ ሥራው የሚጠይቀውን ተግዳሮት በቁርጠኝነት በመቋቋም ዘርቶ አርሞና ከክፉ ጠብቆ የሚያሳድግ ገበሬ የመጀመሪያው በላተኛ እንደሚሆን ሁሉ በአገልግሎቱ የሚደክም/የሚተጋ አገልጋይ የአገልግሎቱ ፍሬ ቀዳሚ ተጠቃሚ ሊሆን ይገባል” ጳውሎስ ጠሊቅ መካሪ …

Read More »

ዊል ስሚዝ እና ቅዱስ ጳውሎስ

ዊል ስሚዝ እና ቅዱስ ጳውሎስ ለፊልም ብዙ ትኩረት የለኝም፣ ካየሁም መርጬ ባይ ነው የምሻው። እናም መርጬ ካየኃቸው ፊልሞች ውስጥ “The pursuit of happines” የሚለውን ዊል ስሚዝ የሚሰራበትን ፊልም በጣም እወድለታለው። አቤት ትወና! እውነት ለመናገር በእሱ የእድሜ ደረጃ እንደዚህ ግሩም አድርጎ የሚተውን አላየሁም፣ አይቻለው እንዴ? አይመስለኝም። ይህ ብቃቱ ያሳመናቸውም ፈረንጆቹ “የጥቁር …

Read More »

ሐሰተኞችን እስከምን ድረስ እንታገሳቸው?

ክፍል አንድ ፍጹማን ግርማ የክርስቶስን ወንጌል ሰባኪዎች እንዳሉ ሁሉ ልዩ ወንጌል ሰባኪዎችም አሉ፤ እውነተኛ ነቢያት እንዳሉ ሁሉ ሐሰተኛ ነቢያትም አሉ፤ እውነተኛ አስተማሪዎች እንዳሉ ሁሉ ሐሰተኛ አስተማሪዎችም አሉ። በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ፈተና ከሆኑት መካከል የስሕተት ትምህርትና እንግዳ ልምምዶች መሆናቸው ተደጋግሞ በመነገር ላይ ያሉ አሳሳቢ ጉዳዮች ናቸው። ባለፉት ዓመታት …

Read More »

እውነትን ለዘለዓለም የሚጠብቅ

በፍጹማን ግርማ ******* “እውነት ምንድነው?” የሚለው ጥያቄ የፍልስፍናዎች ሁሉ ቁንጮ ጥያቄ ነው ይላሉ። ከዛሬ ሁለት ሺ ዓመት በፊት የሮማው ገዢ ንጉስ ጲላጦስ ጌታችን ኢየሱስን በፍርድ ሸንጎ ፊት የጠየቀው የምጸት ጥያቄ ፤ ከክርስቶስ ልደት በፊትም ሆነ በኋላ…ይኸው እስከዛሬ ድረስ ይጠየቃል። ግን በርግጥም…”እውነት ምንድነው?” እውነት ለአንዳንዶች ለአንዱ “እውነት” ማለት ከፍ ያለ የንቃተ-ኅሊና …

Read More »

ሰሚ አልባ ተሃዝቦት

1.ቅጣቱን በመተው ገልጦት ይሆን? ቤተክርስቲያንን አንስቶ የሚወያይ አሊያም የሚያስብብ ሰው ስለተሰገሰጉት ‘በሽታዎች’ የማያነሳ ከሆነ ከእውነት ስልታዊ ማፈግፈግ ላይ መሆን አለበት። ዘመኔን አይቼ እንዲህ የማስብበት ጊዜ ላይ ደርሻለሁ።ምናልባት ያለንበት ሁኔታ እግዚያብ ሔር ቤተክርስቲያንን እየቀጣ ይሆን? አላውቅም። እግዚያብሔር ከቀናው ጋር ቀና ከጠማማው ጋር ደግሞ እንዲያው ነኝ ያለ፣ ስንጣመምበትና ከፍቃዱ ለመራቅ በመፈለጋችንፍላጎቶቻችንን የሚነግሩንን …

Read More »

ከእውነት ርቀህ እየሄድክ ነው?

በአሉላ ጌታሁን Some have wandered away… (1 Timothy 1:6) ከእነዚህም አንዳንዶች ስተው፥ … ወደ ከንቱ ንግግር ፈቀቅ ብለዋል። (1 ጢሞቴዎስ ፩:፮) ማንም ሰው እውነትን በአንድ ጊዜ ለመተው አይወስንም። ብዙውን ጊዜ የሚሆነው፤ ሰዎች ካላቸው እምነት እና እውነት ፈቀቅ ነው የሚሉት፤ ይህም ደግሞ የሚሆነው፣ ቀስ በቀስ፤ በሂደት ነው። ታዲያ ለማፈግፈግ ተጋላጭ እንዳንሆን፤ …

Read More »

ዶክትሪንህን እወቀው

አማኑኤል አሰግድ “ዶክትሪን ይከፋፍላል ባክህ” አለኝ አንድ ወዳጄ። “አስፈላጊ እንደሆነ አውቃለሁ ግን እግዚአብሔር ከዶክትሪናችን በላይ ለድርጊታችን ግድ ይለዋል (God cares far more for our deeds than our creeds)። ዶክትሪን ይከፋፍላል ፍቅር ግን አንድ ያደርጋል” አለኝ በጫዋታ መኸል። ጓደኛዬ ልክ ይሆን? እውነት ዶክትሪን ከፋፋይ ነው? ፍቅርን አንቆ ይዞ ልዩነት አምጪ ተውሳክ …

Read More »